Fana: At a Speed of Life!

በቅርቡ ሕይወቷ ያለፈው የኔልሰን ማንዴላ ሴት ልጅ አስክሬን ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኘ

አዲስ አበባ ፣ሐምሌ 9 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በቅርቡ በ59 ዓመቷ ሕይወቷ ያለፈው የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ  ሴት ልጅ ዚንዲዚ ማንዴላ አስክሬን ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱ ተገለጸ፡፡

በጆሃንስበርግ ሆስፒታል ሕይወቷ ማለፉ የተገለጸውዚንዲዚ ማንዴላ÷ በተደረገላት የኮሮና ቫይረስ ምርመራ  ሕይወቷ ባለፈበት እለት ቫይረሱ እንደተገኘባት ተገልጿል።

ሆኖም የኮሮና ቫይረስ በሽታ ለሞቷ መንስኤ መሆን አለመሆኑ ግልጽ አለመሆኑን የጠቆመው የዚንዲዚ ወንድ ልጅ ዞንድዋ ማንዴላ ÷  ቤተሰቡ የአስክሬን ምርመራ ውጤት እየጠበቀ መሆኑን ለደቡብ አፍሪካ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ገልጿል።

አያይዞም የቀብር ስነስርዓቷ አርብ ጠዋት እንደሚፈጸም አስረድቷል።

ዚንዲዚ ማንዴላ ሕይወቷ ባለፈበት ወቅት በዴንማርክ የደቡብ አፍሪካ አምባሳደር ሆና በማገልገል ላይ እንደነበረችም ነው የተገለጸው

ምንጭ፡- ቢቢሲ እና ዴይሊ ኔሽን

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.