Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በአንድ ቀን 205 ሚሊየን ችግኝ የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በአንድ ቀን 205 ሚሊየን ችግኝ የመትከል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በዛሬው እለት እየተካሄደ ነው።

የችግኝ ተከላውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እና የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ  በባህርዳር ዘንዘልማ አካባቢ አስጀምረዋል።

በክረምቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመትከል ከታቀደው 5 ቢሊየን ችግኝ ውስጥ 1 ነጥብ 75 ቢለየኑ በአማራ ክልል የሚተከል ነው።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፥ የክልሉ መንግስት ለአረንጓዴ አሻራ ስኬታማነት በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል።

በክልሉ ባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞችን የፅድቀት መጠን መከታተያ ካርታ መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል።

በዚህ ክረምት ለሚተከሉት ችግኞችም እስካሁን 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ጉድጓድ መቆፈሩን በመጥቀስ፤ ህብረተሰቡ ራሱን ከኮሮና ቫይረስ እየጠበቀ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጠይቀዋል።

ችግኝ ከመትከል ባሻገር ግን የእንክብካቤ ስራው ትኩረት እንደሚሻ አቶ ተመስገን  ተናግረዋል።

በተያያዘ ዜና የታላቁ ህዳሴ ግድብ እና ጣና ሀይቅን ለመታደግ በአማራ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በጮቄ ተራራ አካባቢ የችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአባይ የውሃ ጋን ተብሎ የሚጠራውን የጮቄ ተራራ በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርስበትን ጉዳት እንዲቋቋም ያለመ ነው ተብሏል።

የሳይንስ ከፍተኛ ሚኒትር ድኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እና በአማራ ክልል የሚገኙ 10 ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮችም በመርሃ ግብሩ ላይ ተሳታፊ መሆናቸው ነው የተነገረው።

በናትናኤል ጥጋቡ እና ስላባት ማናዬ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.