ኢትዮጵያና ሩሲያ የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮጵያና ሩሲያ ረዥም ዘመናት ያስቆጠረውን የሁለትዮሽ ግንኙነት አጠናክረው እንደሚቀጥሉት ተገለፀ።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተረክህን ጋር በዛሬው እለት ተወያይተዋል።
በውይይቱ ወቅትም አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተረክህን የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማትቪየንኮ ለአፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ የላኩትን የእንኳን ደስ አለዎት መልክት ማድረሳቸውንም የፌዴሬሽን ምክር ቤት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመልታል።
በነበራቸው ቆይታም ሁለቱም ሀገራት ከ1897 ዓ.ም ጀምሮ ጠንካራ እና ረጀም ዘመናትን የዘለቀ ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ትስስር እና ግንኘነት እንደነበራቸው አንስተዋል።
ሩሲያ ለኢትዮጵያ ላደረገቸው ዘርፈ ብዙ ድጋፍ አና ትብብር አፈ-ጉባዔ አቶ አደም ፋራህ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያና የሩሲያ ግንኙነት በይጠልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የትብብር እና የመግባብያ ሰነድ ያዘጋጅች መሆኑን የጠቀሱት አምባሳደር ኢቭጄኒይ ተረክህን፥ በሰነዱ ዙርያ በኪጋሊ በሚካሄደው በአለም አቀፉ የፖርላማዎች ህብረት ስንሰባ ላይ ተገናኝተው እንደሚውያዩበት እና ቀጥሎም በሩሲያ -ሞስኮ እንደሚፈራረሙ ተናግረዋል።
በቅርቡም የሩሲያ ፌዴሬሽን እና የገዠው ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር ኪሊም በቅርቡ ኢትዮጵያን እንገሚጎበኘ ጠቅሰው በለሎች የትብብር ማዕቅፎች፣ በቋሚ ኮሚቴዎች አሰራር፣ በመንግስታች ግኑኘት እና በገቢ ክፍፍል ቀመር ዙሪያ የአቅም ግንባታና የልምድ ልውውጥ እንደሚያገርጉትም ገልጻዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።