Fana: At a Speed of Life!

ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን የሚጀምሩት በተለያየ  መደብ ተከፍለዉ ነው-የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ  9 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኋላ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸዉን የሚጀምሩት በተለያየ  መደብ ተከፍለዉ እንደሚሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደ ማሪያም ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ የ2012 የትምህርት ዘመን ማካካሻና ማሟያ  ትምሀርትን ለመስጠት ተቋማት እየሰሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በመሆኑም ከትምህርት አሰጣጥ እስከ ቅበላ የተለያዩ መርሀ ግብሮች ተዘጋጅተዋልም ነው ያሉት ሚኒስትሯ።

የትምህርት አሰጣጡ ሳምንቱም ሙሉ እስከ ምሽት የሚከናወን ሲሆን ከአራተኛ አመት በላይ ያሉና ተመራቂ ተማሪዎች በቅድሚያ እንዲገቡና ትምህርታቸዉን በኦንላይንና በገፅ ለገፅ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል ።

በሌላ በኩል ደግሞ ቀድመዉ የገቡት መርሀ ግብራቸውን እንዳጠናቀቁ ከሶስተኛ አመትና ከዚያ በታች ያሉት ተማሪዎች በተመሳሳይ መንግድ ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ እንደሚደረግ ፕሮፌሰር ሂሩት አብራርተዋል።

አያይዘውም የከፍተኛ ትምህርትም ይሁን አጠቃላይ ትምህርቱ የገፅ ለገፅ ተግባራዊ የሚደረገዉ የኮሮና ቫይረስ በጤና ሚኒስቴርና በሚመለከታቸዉ አካላት  ስጋትነቱ መቀነሱ ሲረጋገጥ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ፕሮፌሰር ሂሩት ይህን በጉጉት የሚጠበቀዉ የገፅ ለገፅ ትምሀርት ለማስጀመርና ወደ ቀደመዉ የኑሮ ስርአት ለመመለስ ወረርሽኙን መከላከል ላይ ተማሪዎች መምህራን እና ሁሉም ማህበረሰብ    ስርጭቱን መከላከል በኩል አሁንም ያለመዘናጋት እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

በሙሀመድ አሊ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.