የትምህርት ሚኒስቴር ከፈረንሳይ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ)የትምህርት ሚኒስቴር ከፈረንሳይ ጋር ዘርፉን ለማጠናከር የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርሟል።
ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) ከፈረንሳይ የአውሮፓ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂያን ኖኤል ባሮት ጋር ተፈራርመዋል።
ስምምነቱ ፈረንሳይ ለኢትዮጵያ የተለያዩ ነጻ የትምህርት እድሎችን ለመስጠት እንዲሁም በሊሴ ገብረማሪያም ትምህርት ቤት የነጻ የትምህርት እድሎችንመርሃ ግብሮችን ለማጠናከር የሚያስችል ነው።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ፕ/ር) በዚሁ ወቅት÷ ኢትዮጵያ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል።
በዚህም አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ይፋ በማድረግ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማጠናከር ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አንስተዋል።
ከፈረንሳይ መንግስት ጋር ዛሬ የተደረሰው ስምምነትም ኢትዮጵያ በትምህርት መስክ የያዘችውን ውጥን እዉን ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።