የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የቼክ ሪፐብሊክ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያን ጁሬካ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብተዋል።
ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር ዘነበ ከበደ እና በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሮቶኮል ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል መላኩ በዳዳ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከመንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በተለያዩ ሀገራዊ፣ ክልላዊ እና አህጉራዊ የጋራ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡