Fana: At a Speed of Life!

የማንቼስተር ደርቢ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር የማንቼስተር ከተማ ክለቦች የሆኑት ማንቼስተር ሲቲ እና ማንቼስተር ዩናይትድ ምሽት ላይ የሚያድረጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

 

ጨዋታው ምሽት 1 ሰዓት ከ30 በኢቲሃድ ስታዲየም የሚከናወን ሲሆን÷ በማንቼስተር ሲቲ በኩል ባለፈው ሳምንት በቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተው ሪኮ ሊዊስ በቅጣት እንዲሁም ሮድሪ፣ናታን አኬ፣ ጆን ስቶንስ እና ማኑዌል አካንጂ በጉዳት ለቡድኑ የማይሰለፉ ይሆናል፡፡

 

የማንቼስተር ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ምንም  አይነት አዲስ ጉዳት እንደሌለ የጠቆሙ ሲሆን÷ ጆኒ ኢቫንስ ከጉዳቱ በማገገም ልምምድ መስራቱን ተናግረዋል፡፡

 

ማንቼስተር ሲቲ ካለፉት 10 ጨዋታዎች አንድ ጊዜ ብቻ በማሸነፍ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ያለ ሲሆን ÷ማንቼስትር ዩናይትድ በበኩሉ ከአዲሱ ፖርቹጋላዊ አሰልጣኝ ጋር ወጥ ያልሆነ አቋም በማሳየት ላይ ይገኛል፡፡

 

በቅርብ አመታት ከፍተኛ ብልጫ በማንቼስትር ሲቲ የተወሰደበት ማንቼስተር ዩናይትድ ወቅታዊውን የሲቲ ደካማ አቋም በመጠቀም ያሸንፋል ትብሎ ሲገመት ማንቼስተር ሲቲ በበኩሉ በከተማው ተቀናቃኝ ዩናይትድ ላይ ያለውን የበላይት ለማስቀጠል ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

 

በሌሎች የሊጉ  የጨዋታ መርሃ ግብሮች 11 ሰዓት ላይ ብራይተን ከክሪስታል ፓላስ ጨዋታቸውን የሚያከናውኑ ሲሆን ÷ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቼልሲ ከብሬንትፎርድ እንዲሁም ሳውዝአምፕተን ከቶተንሃም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

 

ፕሪሚየር ሊጉን  አንድ ቀሪ ጨዋታ እያለው ሊቨርፑል በ36 ነጥብ ሲመራ ጨዋታውን ዛሬ ምሽት የሚያደርገው ቼልሲ በ31 እንዲሁም አርሰናል በ30 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደርጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.