ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአልጀሪያ አቻቸው ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከአልጀሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽና አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በትኩረት መምከራቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያ እና አልጀሪያ በሁለትዮሽና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ትብብር ያላቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡
በቀጣይም ሀገራቱ በኢኮኖሚና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በተጨማሪም የሀገራቱን የጋራ ሚኒስትሮች ኮሚሽን ለማጠናከር ብሎም በነባርና በአዳዲስ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግ ተስማምተዋል፡፡