የአሮሚያ ክልልር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የህዳሴ ግድብን የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌትን በማስመልከት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላፉ።
ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ የህዳሴ ግድብ ከህፃናት እስክ አዛውንቶች ፤አርሶ አደሮች አርብቶ አደሮች ፣ የንግድ ማህበረሰብ፣ የመንግስት ሰራተኞች ባላችሁ ነገር ሁሉ የተሳተፋችሁበትና በመደጋጋፍ ለዚህ ያበቃችሁ የትውልዱ ፕሮጀክት ዛሬ የምስራች ሰምታችኋል ብለዋል።
የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌቱ የተጠናቀቀው ግድቡ ለትውልዱ ሃይል ሊያለማ ዝግጅት ጀምሯል ነው ያሉት።
በአጭር ጊዜ ውስጥም ተርባይኖችን በማንቀሳቀስና ሃይል በማመንጨት የሃገራችንን የጨለማ ምዕራፍ በብርሃን ለመተካት የሃገራችንን ህዝቦች የልማት ጥማት ለማርካት ለአዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
የግንባታ መጓተቶች ተስተውለውበት የነበረው የህዳሴ ግድብ በሀገራችን ሕዝቦች እና በመንግስት ጥረትና ቁርጠኝነት ተመልሶ ሕይወት በመዝራት ወደ ፍፃሜው በፍጥነት እየገሰገሰ ይገኛልም ሲሉ ተናግረዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ዐባይ በፈለገበት መንገድ ሲፈስ የነበረው አሁን በተዘጋጀለት ቦታ ሲያልፍ ለማየት በቅተናል ብለዋል።
አሁንም እንሰራለን ያቀድነውን ሁሉ እናሳካለን ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ይህ ቀን ከምንጊዜውም በላይ ራዕያችን የማይጨናገፍ በተባበረ ክንድ ማሸነፍ እንደምንችል ያሳየንበት ነው በማለት ተናግረዋል።
አቶ ሽመልስ ይሁን እና አሁንም ከፊት ለፊታችን ረጅም መንገድ ነው ያለው፤በውስጣችን ያለው ህብረት ደግሞ የድላችን ምንጭ ሆኖ መቀጠል አለበት ሲሉ አሳስበዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ ካላቸው ትንሽ ነገር ቀንሰው ቦንድ በመግዛት ፤የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በእውቀታቸው እና በጉልበታቸውከግብ ለማድረስ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
አሁንም እጅ ለእጅ ተያይዘን ሀብታችን እና እውቀታችንን በማበርከት ለልማት እና የህዝባችንን ተጠቃሚነት በማልት ጥሪ አቅርበዋል።