Fana: At a Speed of Life!

በየመን የሚስተዋለው የረሃብ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን ተመድ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በየመን የሚስተዋለው የረሃብ አደጋ በከፍተኛ ሁኔታ እያሻቀበ መሆኑን አስታውቋል።

ድርጅቱ ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው ሪፖርት በእርስ በርስ ጦርነት እየታመሰች የምትገኘው የመን ዜጎች በግጭት፣ በድህነት፣ በጎርፍ አደጋ እንዲሁም በበረሃ አምበጣ መንጋ ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል ብሏል።

ከዚህ ባለፈም በቅርቡ በሀገሪቱ የተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ነው የተባለው ።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (ፋኦ) መረጃ እንደሚያሳየው በአሁኑ ወቅት በየመን 20 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ዜጎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል።

ከዚህ ውስጥም 10 ሚሊየን የሚሆኑት የሀገሬው ዜጎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑንም ተገልጿል።

የሀገሪቱ ዜጎች ለከፋ ችግር ከመዳረጋቸው በፊትም የዓለም ሀገራት እና ግብረ ሰናይ ድርጅቶች አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲያደርጉ የመንግስታቱ ደርጅት ጥሪ ማቅረቡን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.