በባህርዳር ከተማ በ760 ሚሊየን ብር የተገነቡ 57 የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በባህርዳር ከተማ አስተዳደር በ760 ሚሊየን ብር የተገነቡ 57 የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የገቢዎች ሚነስትር አቶ ላቀ አያለው ፣የፌደራል ቤቶችና ኮንስትራክሽ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ እና የክልሉ ርዕሰ መስተደድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አማረ አለሙ ÷ በከተማዋ በ760 ሚሊየን ብር የተገነቡ 57 የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ህብረተሰቡ በአግባቡ በመያዝ ሊጠቀምባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።
የከተማ አስተዳደሩ ለአባይ እና ጣና ልማት የሚሆን 1 ነጥብ 6 ሄክታር መሬት መለየቱንም አቶ አማረ አለሙ አንስተዋል ።
ዛሬ በባህርዳር ከተማ አንድ ባለ ሃያ ሁለት እና ሁለት ባለ ስምንት ፎቅ የቢሮ ግንባታ መሰረት ድንጋይ የተቀመጠ ሲሆን÷ይህም የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ቢሮ፣ የባህርዳር ከተማ የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ገቢዎች ቢሮ ግንባታ ለማከናወን ነው ተብሏል።
የገቢዎች ሚኒስትር አቶ ላቀ አያሌው፣ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የሀይማኖት አባቶች በተገኙበት የመሠረት ድንጋዩን የማስቀመጥ ስነስርዓት እንደሚከናወን ተገልጿል።
በናትናኤል ጥጋቡ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።