Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ 24 ሰዓታት 409 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ9 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 6 ሺህ 898  የላብራቶሪ ምርመራ 409 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 933 መድረሱንም የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በትዊተር ገፃቸው ባወጡት መረጃ አመላክተዋል።

ከዚህ ባለፈ የ9 ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ምክንያት ያለፈ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 197 መድረሱንም አመላክተዋል።

በሌላ መልኩ በትናንትናው እለት 139 ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን፥ በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 645 መድረሱም ተገልጿል።

ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ እስካሁን 357 ሺህ 58 ሰዎች ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 11 ሺህ 993 ደርሷል።

አሁን ላይ ቫይረሱ ያለባቸው ሰዎች ቁጥር 6 ሺህ 89 ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ 65 ሰዎች በጽኑ የታመሙ መሆናቸውንም የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

እስካሁን በኢትዮጵያ 5 ሺህ 645 ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገገሙ፤  የ197 ሰዎች ህይወት አልፏል፤ 2 ሰዎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ይታወሳል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.