አቶ አደም ፋራህ በወላይታ ሶዶ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ በወላይታ ሶዶ ከተማ የተለያዩ የሌማት ትሩፋት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸውም በቅርቡ የተጀመረው እና የሌማት ትሩፋት ሥራ አካል የሆነውን የወተት ላሞች እርባታ ያለበትን ደረጃ ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
አቶ አደም በዚህ ወቅት÷ሰው ተኮር ሥራ ሆኖ የተጀመረውን የሌማት ትሩፋት የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ በብልጽግና ፓርቲ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ዘርፍ ሃላፊና የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ አባል ሰማ ጥሩነህ (ዶ/ር) እና የትራስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) መሳተፋቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡