Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በቡራዩ የተገነባውን ኩሪፍቱ ሪዞርት መረቁ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሸገር ከተማ ቡራዩ ክ/ከተማ የተገነባውን ኩሪፍቱ ሪዞርትና የአፍሪካ መንደር መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

አቶ ሽመልስ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ÷የቱሪዝም ዘርፉ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ባለፉት ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል፡፡

መንግሥት የግሉን ዘርፉ በማስተባበር በሀገሪቱ ያሉትን የቱሪዝም መዳረሻዎች ለመስፋፋት ጥረት አድርጓልም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፡፡

ዛሬ የተመረቀው የኩሪፍቱ ሪዞርት ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ዕድገት ትልቅ ሃብት ነው ማለታቸውንም የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

የኩሪፍቱ ሪዞርቶች ባለቤት አቶ ታድዮስ ጌታቸው በበኩላቸው÷የቡራዩ ኩሪፍቱ ሪዞርት እና አፍሪካ መንደር የአፍሪካን አንድነት፣ ብዝሃነት እና ድንበር የለሽ አቅምን ያቀፈ መዳረሻ ነው ብለዋል፡፡

ሪዞርቱ በ163 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈና ሁሉንም የአፍሪካ ሀገራት የሚወክሉ 54 ክፍሎች ያሉት ሲሆን÷ክፍሎቹ በአህጉሪቱ ውስጥ ያለውን ጥበብ፣ ባህል እና ወግ በማንፀባረቅ በጥንቃቄ የተሰሩ ናቸው ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.