Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ምካፓ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቀድሞው የታንዛኒያ ፕሬዚዳንት ቤንጃሚን ምካፓ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

ምካፓ ዳሬሰላም በሚገኝ ሆስፒታል በ81 አመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸውን የሃገሪቱ መንግስት አስታውቋል፡፡

ህልፈታቸውን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ማግፉሊ የሰባት ቀናት ብሄራዊ ሃዘን አውጀዋል፡፡

ምካፓ ህይወታቸው ከማለፉ ውጭ ለህልፈት የዳረጋቸው ምክንያት ግን ምን እንደሆነ አልተገለጸም፡፡

ቤንጃሚን ምካፓ ሃገራቸውን ከፈረንጆቹ 19 95 እስከ 2005 ድረስ በፕሬዚዳንትነት መርተዋል፡፡

የታንዛኒያ ሶስተኛው ፕሬዚዳንትም ነበሩ፡፡

ምንጭ፣ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.