Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ምክር ቤት 15ኛ መደበኛ ጉባኤ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የአማራ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 15ኛ መደበኛ ጉባኤ የፊታችን ሰኞ ይካሄዳል፡፡
ጉባኤው ሐምሌ 20 እና 21 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡

የክልሉ ምክርቤት አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰው ማሞ በሰጡት መግለጫ የአስፈጻሚ አካላት የ2012 በጀት ዓመት የተጠቃለለ ሪፖርት፣ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተሰሩ ስራዎችና በቀጣይ ስለሚሰሩ ስራዎች፣ የ2012 ዓመት ተጨማሪ በጀት ማፅደቅ፣ የ2013 ዓ.ም የካፒታል በጀትና መደበኛ በጀት የጉባኤው ዋና ዋና አጀንዳዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የዋና ኦዲተርና የኦዲተሮች መተዳደሪያ ደንብ እንዲሁም ልዩ ልዩ ሹመቶች እንደሚጸድቁም ነው የተናገሩት፡፡

በሌላ በኩል የክልሉና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግምገማና የክረምት ስራዎች የንቅናቄ ውይይት እያካሄዱ ነው፡፡

የክልሉ ፖለቲካዊና ፀጥታ ሁኔታ፣ የአባይ ጉዳይ፣ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ እንዲሁም አመራሩን ከክልል እስከ ቀበሌ በማጠናከር የተሰሩ ስራዎችን የመገምገምና በቀጣይ የበለጠ ማጠናከር ላይ የሚቻልበት አግባብ የውይይቱ ዋነኛ ነጥቦች ናቸው፡፡

ከዚህ ባለፈም የክረምት ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያም እየተወያዩ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.