Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም ለቆመችለት መርህ ያላትን ታማኝነት ያረጋገጠ ነው – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የታላቁ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም ለቆመችለት መርህ ያላትን ታማኝነት ያረጋገጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በህዳሴ ግድብና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የግድቡ የመጀመሪያ ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዓለም ለቆመችለት መርህ ያላትን ታማኝነት ያረጋገጠ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያውያን ያቀዱትን የሚያሳኩ ሀዝቦች መሆናቸውን ለዓለም ያስመሰከሩበት መሆኑንም አውስተዋል፡፡

በህዳሴ ግድብ ላይ እየተካሄደ ያለው የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት መመራቱ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑንም አስረድተዋል።

በመግለጫው የውሃ ሙሌቱ በድል መጠናቀቁ ኢትዮጵያውያንን በዓለም መድረክ ከፍ አድርጓልም ነው ያሉት።

በሌላ በኩል በባህር ማዶ በችግር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በተመለከተም ከዓለም አቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት እና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁንም ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ ኩዌት፣ ቤሩት እና ከሌሎች ሃገራት 30 ሺህ 87 ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ መመለሳቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ወደ ሃገር ቤት የሚመለሱትን ዜጎች የማቋቋም ስራ እንደሚሰራም አስታውቀዋል፡፡

በሌላ በኩል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኮቪድ19 ሳቢያ ችግር ውስጥ ለገቡ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ እና ስላባት ማናዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.