Fana: At a Speed of Life!

ሚዲያና የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን እና ጀስቲስ ፎር ኦል ፒ ኤፍ ኢትዮጵያ ሚዲያና የጥላቻ ንግግርን በተመለከተ ውይይት አካሂደዋል፡፡

በውይይቱ ላይ የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሚዲያ ሀገር በመገንባትና ትውልድን በማነጽ ረገድ ትልቅ ሚና አለው ብለዋል፡፡

እንዲሁም ሚዲያ የሰላም መሳሪያ የመሆን አቅሙ ትልቅ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ አንጻር ነጻና ገለልተኛ ሆኖ ራሱን በማዳን ሌሎችንም መቅረጽ እንደሚገባ ማሳሰባቸውን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.