Fana: At a Speed of Life!

አንድ ሩጫ ሁለት ክብረ በዓላት – ዘላቂ ክብር የ5ኪሎ ሜትር ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አንድ ሩጫ ሁለት ክብረ በዓላት – ዘላቂ ክብር በሚል የ5 ኪሎ ሜትር ሩጫ በጎንደር ከተማ ተካሂዷል።

ሩጫው የተካሄደው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመትና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ነው፡፡

እስከ 2 ሺህ ሰዎችን ባሳተፈው ሩጫ ላይ 40 ያህል የጎንደር ከተማና የዩኒቨርሲቲው አትሌቶችም ተሳትፈዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመትና የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በተለያዩ ዝግጅቶች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም መከበሩን ይቀጥላል፡፡

በታሪኩ ለገሰ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.