Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ትብብር ለማጠናከር ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና በኢኮኖሚው ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ተገለጸ፡፡

የገንዘብ ሚኒስት አቶ አህመድ ሺዴ ከቻይና አቻቸው ላን ፋ ኦን እና ከቻይና ብሔራዊ ልማትና ሪፎርም ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በዋናነት በሀገራቱ መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብር የበለጠ ማጠናከርን ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተለይም የሁለቱ ሀገራት መሪዎች መግባባት ላይ ደርሰው የተፈረሙ ስምምነቶች ወደ ተግባር መለወጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

በተጨማሪም በውይይቱ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው በኋላ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት እድል ለመመልከት ያለመ ምክክር ማድረጋቸውን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡

በገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ በቻይና የሥራ ጉብኝት እያደረገ ሲሆን፤ በቆይታውም ከተለያዩ ተቋማት ሀላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ ትብብር ዙሪያ ውይይት እያደረገ መሆኑ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.