Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፓኪስታን የፖለቲካ ምክክር መግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያና የፓኪስታን እስላማዊ ሪፐብሊክ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር የሚያስችል የፖለቲካ ምክክር መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና በፓኪስታን ውጭ ጉዳይ ተቀዳሚ ምክትል ሚኒስትር አምባሳደር ሀሚድ አሽገር የተፈረመው ስምምነቱ በዓለም አቀፍና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ነው።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ÷ ኢትዮጵያ ከፓኪስታን ጋር ያላትን ግንኙነት በግብርና፣ ኢንቨስትመንት፣ በንግድ፣ በአቪዬሽን፣ በኢንዱስትሪ፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ማጠናከር እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

ስምምነቱ ሀገራቱ በደቡብ ደቡብ ትብብር እንዲሁም በሁለትዮሽ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች አብረው ለመስራት የሚያስችላቸው መሆኑን መግለፃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ሀሚድ አሽገር በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ እና ፓኪስታን ግንኙነት በሁሉም ዘርፎች እየተጠናከረ መምጣቱን ገልፀው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ጸጥታ እንዲረጋገጥ እያደረገች ያለውን ጥረት አድንቀዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.