Fana: At a Speed of Life!

የለውጡ አዳዲስ እሳቤዎች ለዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር አስችለዋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከለውጡ ወዲህ ገቢራዊ በተደረጉ አዳዲስ እሳቤዎች በየዓመቱ ከአራት ሚሊየን ለሚልቁ ዜጎች የሥራ ዕድል የመፍጠር አቅም መገንባቱን የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የሥራና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ፡፡

የክኅሎትና ፈጠራ መር ኢኮኖሚ ለመገንባት አዳዲስ አሠራሮች መዘርጋታቸውን የገለጹት ሚኒስትሯ÷ ይህም በመስኩ ስኬታማ ሥራዎችን ለማከናወን አስችሏል ብለዋል፡፡

የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅምን ውጤታማ ለማድረግ ተግባራዊ በተደረጉ የብልጽግና እሳቤዎች በየዓመቱ ከአራት ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል አቅም መፈጠሩንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ዜጎች የውጭ ሀገር ኩባንያዎችን ስራ መሥራት የሚችሉበት ዕድል መመቻቸቱን ተከትሎን በአጭር ጊዜ ከ80 ሺህ በላይ የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ነው ያሉት፡፡

ከለውጡ በኋላ በተዘረጋው የድጋፍና ክትትል አሠራር ወደ ውጭ ለሥራ የሚሰማራው ዜጋ ቁጥር እያደገ መምጣቱን ጠቁመው÷ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን የማጠናከርና የቅበላ አቅማቸውን የማሳደግ ሥራ ጎን ለጎን መሰራቱን ገልጸዋል፡፡

በዚህም ተቋማቱ በአጫጭርና መደበኛ የስልጠና መስኮች 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ዜጎችን በየዓመቱ ተቀብለው የማሰልጠን አቅም ፈጥረዋል ነው ያሉት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.