Fana: At a Speed of Life!

ዘላቂ ልማትን ለማፋጠን በቴክኖሎጂ መታገዝ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዘላቂ ልማትና ዕድገትን ለማረጋገጥ በቴክኖሎጂ ውጤቶች የታገዘ ሥራን ማጠናከር እንደሚገባ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር ርዕሰ መሥተዳድር ጌታቸው ረዳ አስገነዘቡ፡፡

በክልሉ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ላይ ያተኮረ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ጉባዔ በመቐለ ከተማ እየተካሄደ ነው።

አቶ ጌታቸው በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር÷ የክልሉን ኢኮኖሚ እና ማሕበረሰብ ዕድገት ለማረጋገጥ የቴክኖሎጂ አጠቃቅምን ማሳደግ እንደሚገባ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በቴክኖሎጂ የታገዘ የውሳኔ ሰጪነትና የአቅም ግንባታ ስትራቴጂን ተግባራዊ ማድረግ ለተጀመሩ ሥራዎች ብሎም ለቀጣይ ዘላቂ ልማትና እድገት ወሳኝ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የቴክኖሎጂ አጠቃቅምን ማጎልበት ለቀጣይ ትውልድ የዕድገት ጎዳና መሰረት መጣል ነው ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.