884 ቀበሌዎች ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ነፃ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 884 ቀበሌዎች ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ነፃ መሆናቸውን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
በአጠቃላይ ከሴት ልጅ ግርዛትና ያለ ዕድሜ ጋብቻ ነፃ የወጡ ቀበሌዎችን ሽፋን 47 ነጥብ 86 በመቶ መሆኑንም ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
ጾታዊ ጥቃትንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከልና ለማስወገድ 224 ግብረ-ኃይሎችን በክልል፣ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ባለፉት ሥድስት ወራት ማቋቋም መቻሉንም ገልጿል፡፡
እንዲሁም ነባር 1 ሺህ 49 ግብረ-ኃይሎችን በማጠናከር በሀገር አቀፍና በክልል ደረጃ ጾታዊ ጥቃትንና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ለመከላከልና ለማስወገድ የተቋቋሙ ግብረ-ኃይል ሽፋንን ከነበረበት ወደ 75 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብሏል፡፡
ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶችና ሕጻናት የተሃድሶ አገልግሎት እየሠጡ ያሉ ማዕከላት ብዛት 20 መድረሱንም ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
በዮሐንስ ደርበው