Fana: At a Speed of Life!

የሕዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መሥራት አለብን- ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መረባረብ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለፁ።

የክልሉ አስፈፃሚ ተቋማት ላለፉት ሁለት ቀናት የግማሽ በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ተገምግሟል፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሯ በዚሁ ወቅት ዕቅዶችን ወደ ተግባር በመቀየር የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት በተጨባጭ ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የልማት ሥራዎችን በአግባቡ ለመወን አሁን ያለው ሰላም ዘላቂና አስተማማኝ እንዲሆን ማድረግ የሁሉም ኃላፊነት ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

የታቀዱ ተግባራት ግባቸውን እንዲመቱ የክትትልና ቁጥጥር ሥራን ማጠናከር ይገባል ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.