ሔር ኢሴ በዩኔስኮ መመዝገቡን በማስመልከት የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ዒሳ ማህበረሰብ ያልተጻፈ ባሕላዊ ሕግ “ሔር ኢሴ” በዩኔስኮ መመዝገቡን በማስመልከት በድሬዳዋ ኢንተርናሽናል ስታዲየም የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው፡፡
በድጋፍ ሰልፉ በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ፣ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር፣የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ እና የተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።
እንዲሁም የሶማሊያና የጅቡቲ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በመርሐ ግብሩ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በተስፋዬ ሃይሉ እና እዮናዳብ አንዱአለም