ኮቪድ 19ን የመመርመር ዐቅማችንን አጠናክረናል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የኮቪድ 19 የመመርመር ዐቅም መጠናከሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ በዛሬው እለት በትዊተር ገፃቸው ባወጡት መረጃ፥ “ኮቪድ 19ን ከመመርመሪያ 1 ሚልየን ኪቶች መካከል የመጀመሪያውን ዙር ዛሬ ተቀብለናል” ብለዋል።
ከዚያም ውስጥ 50 በመቶው በቅርቡ በኢትዮጵያ የማምረት ሥራውን በሚጀምር ሀገር በቀል ኩባንያ አማካኝነት የተለገሰ መሆኑንም አስታውቅዋል።
እነዚህ መመርመሪያዎች ወረርሽኙ በከፍተኛ ሁኔታ መዛመቱን ተከትሎ፣ በሀገር ውስጥ የምርመራ ኪቶችን ለማምረት የሚደረገውን ዝግጅት እስከሚጠናቀቅበት እስከ ጥቅምት 2013 ድረስ ዕለታዊ የምርመራ ዐቅምን ከፍ ለማድረግ የሚያስችሉ መሆኑንም አስታውቅዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።