የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በ510 አውቶብሶች አገልግሎት እየሰጠ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት በ510 አውቶብሶች አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ገለፀ፡፡
ተቋሙ የተመሰረተበትን 10ኛ አመት በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል።
የአገልገሎቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጥላሁን ጂግሶ በዚህ ወቅት ÷ተቋሙ ባለፉት 10 አመታት ራሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን አገልግሎት ሲሰጥ መቆየቱን አንስተዋል።
አሁን ላይም ተቋሙ በ460 የከተማ እና በ50 ሀገር አቋራጭ አውቶብሶች አገልገሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል።
በተጨማሪም ከ10 ሚሊየን በላይ የአዲስ አበባ ታክሲ ተጠቃሚዎች፣ ከ124 ሺህ በላይ የሀገር አቋራጭ ደምበኞች እንዲሁም ከ200 ሺህ በላይ የኮንትራት ተጠቃሚዎች በምልልስ የትራንስፖርት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
በቀጣይም ተቋሙ ራሱን በቴክኖሎጂ በማዘመን የሚሰጠውን አገልግሎት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
በመርሐግብሩ ለረጅም አመታት በህዝብ ትራንስፖርት በአሽከርካሪነት ላገለገሉ አሽከርካሪዎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል።
በሚኪያስ አየለ