Fana: At a Speed of Life!

የኦክስጂን ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ሺኒሌ ከተማ በ137 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የኦክስጂን ፋብሪካ ተመርቆ ተከፈተ።

 

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ሙስጠፌ ሙሀመድ ፋብሪካውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት÷ከለውጡ በኋላ ባሉት ዓመታት በሽንሌ ከተማና አካባቢው 14 ፋብሪካዎች ተገንብተው ስራ መጀመራቸውን ጠቅሰው አካባቢው የክልሉ የኢንዱስትሪ ማዕከል እየሆነ መምጣቱን ተናግረዋል።

 

የተገነባው ኦክስጂን ፋብሪካ በቀን 600 ሲሊንደሮችን የማምረት አቅም እንዳለው በምረቃው ወቅት ተገልጿል።

 

በመርሐግብሩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን፣የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ሙሳ አህመድ፣ የሲቲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና ሌሎች እንግዶች መገኘታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.