የቼክ ሪፐብሊክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ
MF
Melaku Fbc
last seen just now
በፎረሙ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራ ልዑክ ከቼክ ሪፐብሊክ ቢዝነስ እና ኩባንያ ባለቤቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ አምባሳር ምስጋኑ ÷ በኢትዮጵያ እና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር በርካታ እድሎች መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን መፍጠሩን ገልጸው፣ የቼክ ሪፐብሊክ ኩባንያዎችም በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳጋቶ ኩምቤ÷ በኢትዮጵያ ያሉ ኢንቨስትመንት እድሎችን በተመለከተ ለቼክ ሪፐብሊክ ኢንቨስተሮች ገለጻ ማድረጋቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ የተመራው ልዑክ በቼክ ሪፐብሊክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጂሪ ኮዛክ ከተመራው ልዑክ ጋር በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ምክክር አድርጓል፡፡
አምባሳደር ምስጋኑ ÷ ቼክ ሪፐብሊክ ከኢትዮጵያ ጋር ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሀገር መሆኗን አንስተው ይህን ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀና ሁሉን አቀፍ ትብብር ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በኢትዮጵያና በቼክ ሪፐብሊክ መካከል የተካሄዱ የከፍተኛ መንግስት ባለሥልጣናት የጉብኝት ልውውጦች መጨመር በሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አንዱ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል።
ምክትል ሚኒስትር ጂሪ ኮዛክ በበኩላቸው የኢትዮጵያ እና ቼክ ሪፐብሊክን የጋራ ተጠቃሚነት ያማከሉ በርካታ የትብብር ዕድሎች እንዳሉ ጠቅሰው÷ ሀገራቸው ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጁ ናት ብለዋል።
ምክክሩ የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና የተፈረሙ ስምምነቶችም ተግባራዊ እንዲሆኑ ለማስቻል ቁልፍ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል፡፡
ሁለቱ ወገኖች ልዩ ትኩረት ሰጥተውና ተቀራርበው ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም ተጠቁሟል፡፡22:26
Message