Fana: At a Speed of Life!

በነፃ ንግድ ቀጣናው ለመሰማራት ፈቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች ምርት ማስገባት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና በሎጂስቲክና ንግድ ዘርፍ ለመሰማራት ፈቃድ የወሰዱ ባለሃብቶች ምርቶቻቸውን ከጅቡቲ ማስገባት ጀምረዋል፡፡

በዘርፉ ለመሰማራት ፍቃድ ከወሰዱ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሃብቶች መካከል ምሃን ትሬዲንግ የተሰኘ ኩባንያ ከጅቡቲ ወደብ ወደ ነጻ የንግድ ቀጣናው ምርቶችን እያስገባ መሆኑን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

የመሬት ርክክብ ካደረጉ ሰባት ድርጅቶች አንዱ የሆነው ምሃን ትሬዲንግ ምርቶችን በማጓጓዝና በማከማቸት ሥራውን መጀመሩ ተጠቁሟል፡፡

ከዚህ ባለፈም ጭነት የጫኑ ተሳቢዎቹ በመጪዎቹ ቀናት ወደ ነፃ ንግድ ቀጣናው እንደሚገቡ መጠቀሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.