Fana: At a Speed of Life!

የሜካናይዝድ ሃይል ተልዕኮን በብቃት መፈፀም በሚያስችል ዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል – ሌ/ጄ ብርሃኑ በቀለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሜካናይዝድ ሃይል ዝግጁነት የሠራዊቱን ግዳጅ የመፈፀም አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን የሚያመላክትና የሚያጠናክር ነው ሲሉ የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ ገለጹ።

ሌተናል ጄኔራል ብርሃኑ በቀለ በሜካናይዝድ ሃይሉ የግዳጅ ቀጣና ተገኝተው የመስክ ምልከታ አድርገዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የሠራዊቱ የጀርባ አጥንት የሆነው የሜካናይዝድ ሃይል በማንኛውም ጊዜና ቦታ ግዳጅና ተልዕኮን በላቀ ብቃት መፈፀም በሚያስችል የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

እንደተቋም ዘመኑን የዋጀ እና ፕሮፌሽናል ሠራዊት የመገንባት ተልዕኮ ላይ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም መናገራቸውን የመከላከያ ሰራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

በላቀ ብቃት መፈፀም የሚችልና ሁለንተናዊ ብቃትን የተላበሰ የሜካናይዝድ ሃይል አቅምን በዓይነት፣ በብዛትና በብቃት የመገንባት ሒደት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.