በሜታ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡
አደጋው ከጅቡቲ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ የጭነት ተሽከርካሪ ከቆቦ ከተማ ወደ ድሬዳዋ ሲያመራ ከነበረ ዶልፊን ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በተፈጠረው አደጋም የ8 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ሃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ካስዬ አበበ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በሶስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ነው የገለጹት፡፡
በነጌሶ ከድር