ድርጅቱ መንግስት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማርካት እያደረገ ያለውን ጥረት እያገዘ መሆኑን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንግስት የዜጎችን የቤት ፍላጎት ለማርካት እያደረገ ባለው ጠንካራ ጥረት ውስጥ ከፍተኛ ድጋ እያደረገ እንደሚገኝ ያለው አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ገለፀ፡፡
ድርጅቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ የሪል እስቴት ቤቶችን ከ50ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ የቤት ባለቤት ለማድረግ የተሻለ አሰራር ዘርግቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከሶስት ዓመት በፊት መመስረቱን እና 150 ኩባንያዎችን በአንድ ድርጅት ስር እያዋቀረ እንደሚገኝ የገለጸ አፍሪካን ሆልዲንግ ግሩፕ ዜጎችን በ50ሺ ብር ቅድመ ክፍያ የቤት ባለቤት ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክቷል።
በስሩ ከሚገኙት 150 ኩባንያዎቹ መካከል አንዱ በሆነው ጎዶ ሃውሲንግ ኤንድ ስማርት ሪል እስቴት አማካይነት በመንግስትና የግል አጋርነት መርህ 70/30 ፕሮጀክት በመተግበር ላይ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።
ድርጅቱ በሰንጋተራና በተክለሃይማኖት መካከል ከጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ፊት ለፊት በአስር ሺ ካሬ ሜትር ላይ ያዘጋጃቸውን ቤቶች ለቤት ፈላጊዎች ለማስተላለፍ ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 16 ቀን 2017 የሚቆይ ኤክስፖ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ቤት ፈላጊዎች ለአንድ ሳምንት በሚቆዬው ኤክስፖ ላይ በመገኘት ፍላጎትና አቅማቸውን ባገናዘበ መልኩ ለመኖሪያ ቤትና ለሱቆች የተዘጋጁ ቤቶችን ከወዲሁ መምረጥ የሚችሉበትን እድል መፍጠሩን አስረድቷል።
ድርጅቱ በተክለሃይማኖት ዙርያ ለሚገነባቸው ባለ 35 ወለል ዘመናዊ ህንፃዎች ያዘጋጀውን የግንባታ ልማት እቅድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ማስረከቡን ገልጿል፡፡