ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ በጎንደር ከተማ የተሰሩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የከተማና መሰረት ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በጎንደር ከተማ የተሰሩ የተለያዩ ልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡
በጉብኝቱ ሚኒስትሯ በጎንደር ከተማ በምዕራፍ አንድ የተጠናቀቀውን የፒያሳ የኮሪደር ልማትና የፋሲል አብያተ መንግሥት ዕድሳትና ጥገና ሥራን ተመልክተዋል።
በተጨማሪም በፌደራል መንግስት እየተሰሩ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን መጎብኘታቸው ተመላክቷል፡፡
በምናለ አየነው