ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ጥገና ማዕከላትን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት መናኸሪያዎችን እና የጥገና ማዕከላትን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም ተቋሙ አገልግሎቱን ለማሻሻል እየሰራቸው የሚገኙ ሥራዎች አበረታች እንደሆኑ መመልከታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አውቶቡስ ማቆሚያና ማደሪያ ተርሚናሎች ማሻሻያ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ተጠናቅቀው አገልግሎት እንዲሰጡ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
እንዲሁም በመገባደድ ላይ ያሉት የጥገና ማዕከላት ተጠናቅቀው ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲሰጡ ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቁ አሳስበዋል፡፡