Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚገኙ የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ የሚገኙ የሚዲያ አመራሮች እና ባለሙያዎች ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አከናውነዋል።

ህብረተሰቡ ችግኝ እንዲተክል የሚቀሰቅሱ መገናኛ ብዙሃኑ አርአያም እንዲሆን አመራሮቹ እና ባለሙያዎች በጉለሌ እጽዋት ማእከል ችግኝ ተክለዋል።

ችግኝ ተከላ መረሃ ግበሩ ላይም የፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት አመራሮችና የሚዲያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በችግኝ ተከላ መረሃ ግበሩ ላይ የተሳተፉት የፋና ብሮድካስቲንግ አመራሮች÷ ችግኝ መትከል የህዳሴ ግብን በሌላ መልኩ እንደመደገፍ ይቆጠራል ብለዋል።

ችግኝ መትከል ብቻውን ግብ ስላልሆነ የተተከሉትን መንከባከብ የሁሉም ኃላፊነት ሊሆን እንደሚገባውም ነው የገለጹት ።

ለዚህም ሚዲያዎች ልማት ላይ ከፍተኛ የሆነ ፋይዳ ስላቸው ሀገራዊ ንቅናቄ ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ተብሏል።

በቅድስት ብርሃኑ

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.