የሞሪታኒያ ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሞሪታኒያ ፕሬዚዳንት መሀመድ ኦሊድ ጊዞኒ በ38ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የማዕድን ሚኒስትር ሀብታሙ ተገኝ (ኢ/ር) አቀባበል አድርገውላቸዋል።
38ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎቸ ጉባዔ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል፡፡