Fana: At a Speed of Life!

የፍትህ ሚኒስቴርና የክልል ፍትህ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የፍትህ ሚኒስቴር እና የክልል ፍትህ ቢሮዎች የጋራ ጉባኤ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ “ጠንካራ የፍትህ አካላት ቅንጅት ለተረጋገጠ የሕዝብ አመኔታ” በሚል መሪ ሃሳብ መካሄድ ጀምሯል።

በጉባኤው የፍትህ ሚኒስትር ሐና አርአያስላሴ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድን ጨምሮ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እየተሳተፉ ነው።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባኤ የጋራ የሆኑ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት የሚደረግባቸው ሲሆን÷የቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ መባሉን የፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.