ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) ከመንግስታቱ የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ ፕሬዚዳንት ጄፍሪ ዲ ሳች (ፕ/ር) ጋር ተወያይተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የዘላቂ ልማት ማዕከል ዳይሬክተርና የተባበሩት መንግስታት የዘላቂ ልማት መፍትሔዎች ኔትዎርክ ፕሬዚዳንት ጋር መወያየታቸውን ተናግረዋል፡፡
በውይይታቸውም ከዕድገት ጋር በተያያዙ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ገልጸው ÷ ጄፍሪ ዲ ሳች (ፕ/ር) አሁንም የኢትዮጵያ ጥሩ ወዳጅ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
ውይይቱ ሁለተኛ ቀኑን በያዘው የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ መደበኛ ጉባዔ ጎን ለጎን ነው የተካሄደው፡፡