Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደምን የንግድ ትብብር የሚያጠናክር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ፣ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን እና አሴት ግሪን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደምን የጋራ የንግድ ትብብር የሚያጠናክር የኢንቨስትመንት ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከዩናይትድ ኪንግደም አቻቸው አንጄላ ሬይነር ጋር መወያየታቸውን አንስተዋል፡፡

በዚህ ወቅትም የኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደምን የጋራ የንግድ ትብብር የሚያጠናክር የኢንቨስትመንት ስምምነት መፈራረሙን አንስተዋል፡፡

የተከናወነው የአክሲዮን ባለድርሻ ስምምነት ኢትዮጵያና ዩናይትድ ኪንግደም በግብርናው ዘርፍ የተቀናጀ የሰብል ልማት እና የወተት ተዋጽኦ ምርት እና ንግድ እንዲያከናውኑ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

ስምምነቱ ከፍተኛ ውጤት እየተመዘገበበት ለሚገኘው የግብርና ሴክተር ተጨማሪ አቅም ከመገንባት ባለፈ ለዜጎች የስራ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ስምምነቱ ዘመናዊ እና አስተማማኝ የግብርና ስራ እንዲከወን እንዲሁም የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስተመንትን የሚያበረታታ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.