ፕሬዚዳንት ታዬ በናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 20፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢፌዲሬ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ በናሚቢያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ።
ፕሬዚዳንት ታዬ በጽሑፍ ባስተላለፉት የሃዘን መግለጫ÷ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ሳም ኑጆማ ናሚቢያን “መካከለኛ ገቢ ወዳለው ሀገር ያሻገሩ መሪ ተብለው ይታወሳሉ” ሲሉ አስፍረዋል።
ፕሬዚዳንት ታዬ አክለውም ሳም ኑጆማ የናሚቢያ መስራች አባት እና ሀገራቸውን የቀየሩ መሪ ነበሩ ማለታቸውን የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።