Fana: At a Speed of Life!

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን መረቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባውን አዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ማዕከልን በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል።

15ሺህ ካሬ የውጪ ሁነት ማስተናገጃ ቦታ ያለው የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማእከል ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴል፣ ሪስቶራንቶች፣ የስፖርት፣ የጤና፣ የመዝናኛ እና ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫን ያከተተ ግዙፍ ማዕከል ነዉ።

ከዚህም ባሻገር፣ በአንድ ጊዜ እስከ 2ሺህ ተሽከርካሪዎችን ማቆም የሚችል ፓርኪንግ ያለዉ ሲሆን ፥ የለሚ ፓርክ እና በቀጥታ ከአየር መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሰፊ የመንገድ መሰረተ-ልማትም ከማዕከሉ ጋር ተያይዞ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡

ይህም ኢኮኖሚውን የሚያነቃቃ፣ ሰፊ የስራ እድል የሚፈጥር ከመሆኑ በላይ እንግዶች ሲመጡ ያለምንም እንግልት ሁሉንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ እንዲያገኝ ተደርጎ የተሰራ ማዕከል መሆኑንም ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.