Fana: At a Speed of Life!

የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በዚህ ዓመት ተጠናቅቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ ይጀምራል – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ግንባታ በአስደናቂ የማጠናቀቂያ የግንባታ ምዕራፍ ላይ ይገኛል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፥ ስታዲየሙ ባለፈው ሐምሌ ላይ ስንመጣ ከነበረው ገፅታ በእጅጉ ተለውጦ ተመልክተናል ብለዋል።
ምድረ ግቢው የተሻለ አምሮ፣ የተመልካች ወንበሮች ገጠማ እየተፋጠነ፣ ሳሩ ተተክሎ እና ሌሎች የውስጥ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ነው ያሉት።
የስታዲየሙ ግንባታ በሁሉም መሠረተ ልማቶች የካፍ እና ፊፋን ዓለም አቀፍ ደረጃ ጠብቆ በመጨረሻው የግንባታ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አመልክተዋል።
ግዙፉ የባህር ዳር ስታዲየም ሀገራችን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን እንድታስተናግድ ዕድል የሚፈጥር ነው ሲሉም ገልጸዋል።
በተጨማሪም ለባህር ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት፣ የገቢ ምንጭና የስፖርት ዘርፉ መነቃቃት የሚኖረው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው ብለዋል።
በዚህ ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቅቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንደሚጀምር በጉብኝታቸው መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.