Fana: At a Speed of Life!

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለተኪ ምርት ትኩረት መስጠት እንደሚገባ አሳሰቡ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ለተኪ ምርት ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ግባችን እንዲሳካ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አሳሰቡ፡፡

የአማራ ክልል አምራች ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ከፍተኛ መነቃቃት ማሳየቱን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በክልሉ በነበራቸው ቆይታም፤ የአማራ ብረታ ብረት ኢንዱስትሪ እና ማሽን ቴክኖሎጂ ልማት ኢንተርፕራይዝ የሥራ ሂደትን መጎብኘታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ኢንተርፕራይዙ በተሰማራባቸው የብረት ማቅለጥ፣ የማሽነሪ ምርት፣ የኮሪደር ዲች ከቨሮች፣ ስማርት ፖሎች ማምረት፣ የትራንስፎርመር እና የእርሻ መሣሪያዎችን በመገጣጠም ለክልሉ የልማት ሥራዎች መፋጠን ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡

በተለይም ተኪ ምርቶችን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የውጭ ምንዛሪን ከማዳን ባለፈ፤ የልማት ሥራዎች በግብዓት እጥረት እንዳይስተጓጎሉ እያገዘ መሆኑን አንስተዋል፡፡

አምራቾች ለተኪ ምርት ትኩረት በመስጠት ሀገራዊ ግባችን እንዲሳካ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም አሳስበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.