Fana: At a Speed of Life!

የኮሪደር ልማቱ ለዜጎች ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን ይፈጥራል – አቶ ኦርዲን በድሪ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኮሪደር ልማት ሥራው የሐረር ከተማን ዕድገት ከማሳለጥ ባለፈ ለዜጎች ዘመናዊ የከተሜነት የአኗኗር ዘይቤን ይፈጥራል ሲሉ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በጁገል ቅርስ ውጫዊ ክፍል እየተከናወነ የሚገኘውን የኮሪደር ልማት፣ የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል፡፡

በዚሁ ወቅትም የልማት ሥራዎቹ አካባቢውን በማስዋብ የተሻለ ገፅታን ያላብሳሉ ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ አመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በቱሪዝም ዘርፍ ተጨማሪ ዐቅም በመሆን፤ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የልማት ሥራዎቹ ፋይዳ የጎላ ነው ብለዋል፡፡

የኮሪደር ልማት ሥራውን በጥራት እና ፍጥነት በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.