Fana: At a Speed of Life!

ድርቅን በዘላቂ ልማት ለመቋቋም የተጀመረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በምሥራቅ ቦረና ዞን ድርቅን በዘላቂ ልማት ለመቋቋም የተጀመረው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የዞኑ ግብርና ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

ዞኑ በክልሉ ዝናብ አጠርና በተደጋጋሚ ድርቅ ከሚጠቁ አካባቢዎች አንዱ እንደመሆኑ የክልሉ መንግሥትም ድርቁን ለመቋቋም የሚያስችሉ የልማት ኢንሼቲቮችን ቀርጾ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

በምሥራቅ ቦረና ዞን ግብርና ጽ/ቤት የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ባለሙያ ወይዘሮ ጌጤነሽ ታደሰ እንደገለጹት÷ የዝናብ እጥረትንና ድርቁን ለመቋቋም በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።

የልማት ስራው በሁሉም ወረዳዎች 99 ተፋሰሶችን መሰረት ያደረገና 63 ሺህ 972 ሄክታር መሬት የሚያካልል እንደሆነ ተገልጿል፡፡

እስካሁን በተደረገ እንቅስቃሴም 11 ሺህ 738 ሄክታር የግጦሽ ሳር መሬት መከለሉንና 12 ሺህ 486 ኪሎ ሜትር የማሳና የተራራ ላይ እርከን መሰራቱን ገልጸዋል።

የተፋሰስ ልማቱን በእጽዋት ለመሸፈን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኝ የማዘጋጀት ስራም እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በአፈርና ውሃ ጥበቃ ልማት ስራው በመሳተፍ ላይ ከሚገኙ 186 ሺህ 868 ህዝብ ውስጥ 81 ሺህ 613 የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.