Fana: At a Speed of Life!

ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 28፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ጋር በጁባ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተላከን መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት ማስረከባቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ ልዑክ ለይፋዊ ሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ጁባ መግባቱ ይታወቃል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.