Fana: At a Speed of Life!

በ6 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ በረራ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ትናንት ከምሽቱ 5 ሠዓት ጀምሮ በሥድስት ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ሙሉ በሙሉ በሴቶች ብቻ በረራ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን የኤርናቪጌሽን አገልግሎት ዘርፍ እነዚህን ሥድስት ዓለም አቀፍ በረራዎች በሴቶች ብቻ እንዲስተናገዱ ማድረጉን በማኅበራዊ ትርሥሥር ገጹ አስታውቋል፡፡

በረራዎቹ በሴቶች ብቻ እንዲሸፈኑ የተደረገው፤ ዓለም አቀፉን የሴቶች አስመልክቶ መሆኑም ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.