Fana: At a Speed of Life!

ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን እያከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 29፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በጅማ እያከበረ ነው፡፡

የመከላከያ ሠራዊት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ዳይሬክተር ብርጋዲየር ጀኔራል ሁሉሀገርሽ ደረስ እንዳሉት÷ ሴቶች ከወንዶች እኩል ጀግንነታቸውን አሳይተው በቆራጥነት ኢትዮጵያን በመጠበቃቸው ሊወደሱ ይገባል፡፡

ሴቶች በተፈጥሮ የተሰጣቸውን ብልህነት ተጠቅመውና ብቃታቸው ተደምሮበት ሀገርን ከጠላት ሲጠብቁ መቆየታቸውን አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም የሌሎች ሴቶችን መብት በማስጠበቅ ለሀገር ሁለንተናዊ እድገት አስተዋፅዖ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የዳሎል ማዕከላዊ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀነራል ዘውዱ በላይ በበኩላቸው ÷ የሴቶች ቀንን ስናከብር ስለሰላም የሴቶችን ሚና በመዘከርና የሴቶች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ነው ብለዋል።

በአብዱረህማን መሀመድ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.